እንኳን ወደ ቤተፋጌ አለም አቅፍ ቤተ ክርስቲያን ድረ-ገጽ በሰላም መጡ!

ወደ ቤተፋጌ አለም አቅፍ ቤተ ክርስቲያን ድረ-ገጽ እንኳን በደህና መጡ። በድረ-ገጻችን ላይ ቤተ ክርስቲያናችንን ራእይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች፤ እንደዚሁም የእምነት መግለጫና የቤተ ክርስቲያኒቱን ባለራዕይና መሪ ነብይ መስፍን በሹን አጨር ታሪክ ያገኛሉ። በየጊዜውም የሚመጡ ፕሮግራሞችንም በዚህ ድረ-ገጽ ያገኛሉ። የነብይ መስፍን አገልግሎት ስብከት፣ ጸሎት፣ ትንቢት፣ ነጻ መውጣት፣ ፈውስ፣ ምስክነት እና አምልኮ ቪዲዮዎችንም በቀላሉ ያገኛሉ። ቀስ በቀስም የአገልግሎት ክፍሎቻችን የሚሰጡአቸውን አገልግሎቶች ሁሉ በሰፊው ወደ እርስዎ እንደምናደርስ ተስፋ እናደርጋለን። ከአለም ዙሪያም ያላችሁ ወገኖች እንድትጎበኙን እጋብዛችኋለሁ። የጌታ ዳግም ምጽአት በደጅ ነው። ይምጡ! አብረን እንሥራ። ሕዝባችንን እና ዓለሙንም ሁሉ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንድረስ። ያድናል ይታደግማል! እግዚአብሔር ይባርክዎ!

ነብይ መስፍን በሹ

የቤተ-ፋጌ አለም አቅፍ ቤተ ክርስቲያን መስራች እና ባለራዕይ

ከነብይ መስፍን ጋር ይጸልዩ!

የቤተ-ፋጌ አለም አቅፍ ቤተ ክርስቲያንራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች

ራዕይ

ብዙዎች ወደ ክርስቶስ የወንጌል እውነት መጥተው፣ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የታጠቁ እና ሁለንተናዊ አገልግሎት የሚሰጡ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ሆነው ማየት።

ተልዕኮ

አማኞችን ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ማድረግ እና ለሁለንተናዊ አገልግሎት ማስታጠቅ።

እሴቶች

ፍቅር፣ አንድነት፣ ቅድስና፣ አጋርነት፣ ፆም እና ጸሎት፣ አገልጋይነት፣ ጽድቅ እና ፍትሕ እና ግልጽነት

እግዚአብሔር ይመልስልኃል

እግዚአብሔር ይመልስልኃል

11 January, 2020Posted In : Preaching

Preaching by prophet Mesfin @ Hawassa Bethphage International Church READ MORE

ምስክርነት

23 August, 2019Posted In : Testimony

READ MORE

"እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል" ዘፍጥረት 50:24

JOIN TODAY

 • circle

  እግዚአብሔር አባትህ ዙርያህን የከበቡትን እንዳትሄድ እንዳትፈጠን የጠፈሩክን እንደ  ጉም ይበትንልሃል። ከፊት ለፊትክ እንደ ሀያል የቆሙ ሌሎችን እንዳስቆሙ ታርክ የመሰከረላቸው መሰናክሎች እግዚአብሔር አባትህ በሀይል ሳይሆን እንደ ትብያ ይበትናቸዋል።

  Prophet Mesfin
 • circle

  “አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች። “

  ኢሳ 61: 10
 • circle

  ቤቴል ቲቪ አሁን ስርጭቱን መጀመሩን እያበሰርናችሁ የሚከተለውን መረጃ በመሙላት ይከታተሉ።

  Frequency- 10815; Symbol Rate- 27500; Polarization- horizontal

  Bethel TV