የቤተ – ፋጌ አለም አቅፍ ቤተ ክርስቲያን የእምነት መግለጫ

1 መጽሐፍ ቅዱስ

ስድሳ ስድሰቱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍቶች በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው የተገለጠ እውነተኛ ስህተት የማይገኝበት የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለን ስናምን ለእምነችንና ለዕለት ዕለት ኑሮአችን ብቸኛ የሕይወታችን መመሪያ አድርገን እንቀበላለን። ዕብ 4:12 ፤ 2 ጴጥ 1:20 – 21 ፤ 2 ጢሞ 3:15 – 16 .

2 ሥላሴ

በሥላሴ በአንድ አምላክ ስናምን ይህ አንዱ አ ምላክ በሦስት አካል ውስጥ የተገለጠ መሆኑንና እነዚህ ሦስቱ አካሎች እግዚአብሔር አብ፤ እግዚአብሔር ወልድ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሲሆኑ በስልጣን፣ በኃይል፣ በባሕሪ እኩል መሆናቸውን እናምናለን። ማቴ 28: 18 – 20 ፤ 2 ቆሮ 13:14 ፤ ቆላ 2:9 ፤ 1 ዮሐ 1:7 ፤ ዘዳ 6:4 .

3 የሰው ልጅ ውድቀትና መዳን ( ድኅነት )

ሀ . የሰው ልጅ ውድቀት፦ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መልክና በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረ ሲሆን፣ ሲፈጠር ከኃጥያት ነፃ በጽድቅ የሚኖር ሆኖ መፈጠሩን ስናምን እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ዓላማው እርሱን ለማክበርና ከእርሱ ጋር ኅብረት እያደረገ የእርሱን ዓላማ በምድር እንዲያስፈጽም ነው። ነገር ግን በአዳምና ሔዋን ኃጢያትና አለመታዘዝ ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ያ ለው ኅብረ ት በመበላሸቱ የመንፈስና የሥጋ ሞት ሞተ። ከእግዚአብሔር ቁጣ በታችም በመሆኑም በራሱ መንገድ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ወይም መመለስ እንደማይችል ሲነገረው ሙሉ ለሙሉ ተስፋ የሌለው ሆነ፣ ይህም ካለመታዘዝና ከኃጢያት ተፈጥሮ የተነሣ የሰው ልጅ ሁሉ ለኃጢያት ለሞትና ለሠይጣንም ተገዥ ሆነ። ዘፍ 1:26 – 27 ፤ ዘፍ 3:1 – 19 ፤ ሮሜ 3:23 ፤ ሮሜ 5:10 – 12 ፤ ሮሜ 6:23 ፤ 1 ቆሮ 2:14 ፤ ኤፌ 2:1 – 3

4 የደኅንነት መን ገ ድ

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል ጌታና አዳኝ አድርጎ ማመንና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረትን ለማድረግ ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን ጸጋ መቀበልና ማመን ነው። ዮሐ 14:6 ፤ ኤፌ 2:8 – 9 ፤ ቲቶ 3:5 4.5

5 የውኃ ጥምቀት

የውኃ ጥምቀት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ስም በውኃ ውስ ጥ በመጥለቅ ከክርስቶስ ጋር መሞታችን ከእርሱም ጋር መነሣታችን ሕጉንና ትእዛዙን ሁሉ ለመጠበቅ በሰዎች ፊት በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚፈጸም ሥርዓት ነው። ይህን ጥምቀት የሚጠመቀው ሰው፣ በራሱ አውቆ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል ጌታና አዳኝ አድርጎ በመቀበል ሲሆን ከቅዱሳንም ጋር ኅብረት ለመፍጠር የሚፈጸም ሥርዓት መሆኑንም እናምናለን። ማቴ 28:18 – 20 ፤ ሮሜ 6:6 – 14

6 የጸጋ ስጦታዎች

ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል ጌታና አዳኝ አድርገው ሲቀበሉ እግዚአብሔር በክርስቶስ ላመኑት ሁሉ የጸጋ ስጦታዎችን እንደሚሰጥ እናምናለን። እነዚህም የጸጋ ስጦታዎች እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ እንጂ እንደ አማኙ ፍላጎትና ፍቃድ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ እንደፈቀደ ሲሆን ከጥቂቶቹ የጸጋ ስጦታዎች በ ቀር ብዙዎች የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽና ሰዎችን ለማገልገል የተሰጠን ስጦታዎች መሆናቸውን እናምናለን። ሉቃ 24:49 ፤ 1 ቆሮ 12:1 – 31 ፤ ሮሜ 12:4 – 8 ፤ ኤፌ 4:11 – 13

8 የመንፈስ ቅዱስ መሞላትና ምልክት

የመንፈስ ቅዱስ መሞላት ምልክት ነው ብለን የምናምነው ሦስት ምልክቶች ሲሆን እነዚህም፦

1 ኛ . ወዲያውኑ የሚታይ በአዲስ ቋንቋ መናገር

2 ኛ . ውሎ እያደር የሚታይ የመንፈስ ቅ ዱስ ፍሬ

3 ኛ . ለሰዎች የሚታይ የሕይወት ምስክርነትና አገልግሎት። ( የሐዋ 1:8 ፤ የሐዋ 2:4 ፤ማቴ 1:12 ፤ ማቴ 5:16 )

9 ቅድስና

ቅድስና ለእግዚአብሔር መለየት ወይም ከኃጢያት መራቅ መሆኑን ስናምን ይህ ቅድስና በውስጥ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በቃልና በጸሎት የሚደረግ መንፈሳዊ መሠራት ብለን ስናምን በውጭ ደግሞ እግዚአብሔር በማይከብርበት ሌላውን ሰውንና እራሳችንን ከሚጎዳ ማንኛውም ነገ ር ተለይተን ክርስቶስን በመምሰል የምንኖረው የመስዋዕትነት ኑሮ ነው። የሐዋ 1:32 ፤ 1 ቆሮ 1:2 ፤ 1 ቆሮ 6:11 ፤ 2 ተሰ 2:13 ፤ ዕብ 2:11 ፤ 1 ጴጥ 1:2 ፤ ዮሐ 17:17 – 19

10 ጽድቅ

በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን ሙሉ በሙሉ የኃጢያት ይቅርታ እንደሆነ እናምናለን፤ ይህም ክርስቶስ ለኃጢአት ዋጋን በመክፈሉ እግዚአብሔር የእኛን ኃጢአት በክርስቶስ ላይ እንዳደረገና የእርሱን ጽድቅ ለእኛ በመስጠቱ ጻድቃንና ቅዱሳን ተብለን እንድንጠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን ምህረትና ይቅርታ ነው። ሉቃ 13:3 ፤ የሐዋ 2:38; 3:19; 10:43 ፤ ሮሜ 3:26 ; 10:9 – 10

11 ቤተ ክርስቲያን

በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ አምነው በመንፈስ ቅዱስና በውኃ የተጠመቁ የአማኞች ኅብረት ስትሆን ቤተ ክርቲያንን የመሠረታትና በባለቤትነትም ደግሞ የሚቆጣጠራት ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እናምናለን። የአማኞች ድርሻ ለቃሉና ለመንፈስ ቅዱስ በመታዘዝ እርስ በእርሳቸው በመዋደድ የክርስቶስን ታላቁን ተልእኮ ለመፈጸም በአንድነት የተደራጀ አካል መሆኑን እናምናለን። ቤተ ክርስቲያን ከእስራኤል የተለየች በብሉይ ኪዳንም ምስጢር ሆና የቆየች የአሕዛቦችና የአይሁዶች እርቅ የተፈጸመበትና ነገድን ቋንቋን ዘርንና አገርን ሳትለይ ለሁሉም በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ለሰው ልጆች የእግዚአብሔርን ምህረትና ይቅርታ ለማወጅ በምድር ላይ ክርስቶስን በመወከል አሳቡን የምታስተላልፍ አካል ነች። ኤፌ 1:22 – 23; 2:19 – 22 ፤ ዕብ 12:23 ፤ ማቴ 16:16 – 18

12 መለኮታዊ የአገልግሎት ጥሪ

መለኮታዊ የአገልግሎት ጥሪ ብለን የምናምነው፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ከሆኑት ተከታዮች ሐዋርያት ብሎ አስራ ሁለቱን እንደሾማቸው ሁሉ፣ የቤተ ፊ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ሁለት አይነት ጥሪ እንዳለ ታምናለች፤ 1 ኛ ዓለምን በወንጌል የመድረስ የሁሉ አማኝ ጥሪ እንደሆነ ስታምን፣ ፪ኛ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽና የክርስቶስን አሳብ ቅዱሳን እንዲፈጽሙ ለማድረግ፣ አምስቱ የቤተ ክርስቲያን አመራር አገልግሎት ስጦታዎች ለቤተ ክር ስቲያን እንደሰጠና እነዚህ ስጦታዎች የተሰጣቸው አገልጋዮች በሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዲያገለግሉ ለአገልግሎት መለየት መለኮታዊ ጥሪያቸውን ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰዎች በረከት ታደርጋለች። እነዚህም አምስቱ የአገልግሎት ቢሮዎች፦ ሀ ) ሐዋርያነት ለ ) ነቢይነት ሐ ) መጋቢነት መ ) አስተማሪነት ሠ ) ወንጌላዊነት ናቸው። እነዚህን አምስቱ የአገልግሎት ስጦታዎች ዛሬም እንደሚሰሩና ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ እንደሆኑ በማመን ይህ ስጦታ ያላቸውን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት መለኮታዊ ጥሪ ያላቸው መሆኑን በማመን ለአገልግሎት ትሾማለች። ይህ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ሹመት ሂደቱ ተጠሪው የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ጥሪ እንዳለው ለቤተ ክርስቲያን ሲያመለክት ቤተ ክርስቲያንም በቂ የቃሉ እውቀትና የአገልግሎት ፍሬን በማየት ለአገልግሎቱ ትሾማለች። ማቴ 28:18 – 20 ፤ ማር 16:18 – 20 ፤ ኤፌ 4:11 – 13

13 መለኮታዊ ፈውስ

የቤተ – ፋ ጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የሰው ልጆች የመንፈስና የሥጋ በሽታ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም በሚደረገው ጸሎት ሙሉ በሙሉ መፈወስ እንደሚችል ስታምን፤ የኃጢአትን በሽታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በማመንና ንስሐ በመግባት ብቻ እንደሆነ ታምናለች። ኢሳ 53:4 ፤ ማቴ 6:16 – 17 ፤ ያዕ 5:14 – 16

14 የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ተስፋና የክርስቶስ የፍርድ ወንበር

ይህ የምህረት ዓመት አንድ ቀን እንደሚያበ ቃና ክርስቶስ ኢየሱስ ዳግም ተመልሶ ወደዚህ ምድር እንደሚመጣ የቤተ ፋጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ታምናለች። ይህ ዳግም ምጽአቱ እውነተኛ አማኞቹ የሚነጠቁበት በጌታ የሞቱትም ከሙታን የሚነሱበት አመጣጥ ይሆናል። ዮሐ 6:39 ፤ ዮሐ 14:1 – 3 ፤ 1 ቆሮ 15:51 – 53 ፤ 1 ተሰ 4:13 – 16 ፤ 1 ተሰ 5:1 – 11 በዚህ በመጀመሪያው የክርስቶስ ኢየሱስ ዳግም ምጽአት በክርስቶስ ኢየሱሱ ያላመኑት ምድር ላይ ሲቀሩ የሞቱት ደግሞ በሲዖል ይቆያሉ። ራእይ 20: 13 – 17 ይህ የመጀመሪያው የአማኞች ትንሣኤ በጌታ አምነው በሕይወት ያሉት የትንሣኤን ሥጋ በመልበስ ለሰባት ዓመት ከጌታ ጋር በሰማይ ላይ የሚቆዩ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ በመጀመሪያው ሦስት አመት ተኩል በምድር ላይ በሚኖሩበት ዘመን የሠሩት ሥራ የሚገመገምበትና ጥሩ ላደረጉት የሚሸለሙበት ጥሩ ያላደረጉ ደግሞ የሚያዝኑበት የክርስቶስ የፍርድ ወንበር ተብሎ የሚጠራ ነው 1 ቆሮ 3:10 – 15 ፤ 2 ቆሮ 5:10 ፤ የሚቀጥለው ሦስት ዓመት ተኩል የበጉ ሠርግ ተብሎ ይጠራል ማቴ 26:29 ሙሉ ለሙሉ የሚፈጸምበት ይሆናል።

15 ሰባቱ የመከራ ዘመን

ቤተ ክርስቲያን ከምድር ወዲያውኑ እንደተነጠቀች ኃሰተኛ ነብይ፣ አውሬው፣ ኃሰተኛው ክርስቶስ ይህቺን ዓለም ለሰባት ዓመት እንደሚገዛ፤ በእነዚህ ሰባት ዓመታት ውስጥ የአለም ሕዝብ ሁሉ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና በምጣኔ ሀብት ( ኤኮኖሚ ) አን ድነትን በመመስረት ዓለም የምትተዳደር መሆኗንና ስድስት ስልሣ ስድስት (666) የአውሬው ቁጥር በምድር ሙሉ በሙሉ የሚሠራበትና ምድርም ሙሉ በሙሉ በሰይጣን ቁጥጥር ሥር የምትሆንበት ጊዜ እንደሆነ የ የቤተ ፋጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ታምናለች። ዳን 9:24 – 27 ፤ማቴ 24:15 – 31 ፤ ማቴ 25:31 – 46 ፤ ራእይ 20:13 – 17

16 የክርስቶስ ሺህ ዓመት ንግሥና

ከሰባት ዓመት በምድር የሰይጣን አገዛዝ ዘ መን በኋላ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሺህ ዓመት ንግሥንና በሥጋው ወደ ምድር እንደሚመጣና ለሺህ ዓመት ምድርን በንጉሥነት እንደሚገዛ ሁሉ በሺ አመት መጨረሻም ከሙታን የተነሱት እና በህይወትም ያሉት የሰው ልጆች ሁሉ የመጨረሻው የሕይወታቸውን ሥፍራ የሚነግራቸው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነና በእርሱ ያመኑት ወደ ዘላለም ህይወት፤ በጌታ ያላመኑት ለሰይጣን ወደ ተወሰነው የዘላላም እሳት ባሕር የሚሄዱበት ፍርድ እ ንደሆነ እናምናለን ። ዳን 12:2 ፤ ማቴ 25:41 – 46 ፤ ሉቃ 16:19 – 26 ፤ ዮሐ 5:28 – 29 ፤ 2 ተሰ 1:7 – 9 ፤ ራእይ 20:7 – 10

17 የነጩ ዙፋን ፍርድ

የክርስቶስ ኢየሱስ ሺህ ዓመት ንግሥና እንዳበቃ ሰይጣን ከእስራት እንደሚፈታና የአለምን ሕዝብ ነገስታቶችን ሁሉ በማስተባበር በክርስቶስና በኢየሩሳሌም ላይ የመጨረሻውን ታላቅ ውጊያ እንደሚያካሂድና በጦርነቱም ተሸንፎ ለዘላለም እርሱንና በሥራውም ከተ ባበሩት መለአክት እና ሰዎች ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ እሳት ባሕር ይገባል ይህም የመጨረሻው የነጩ ዙፋን ፍርድ ተብሎ እንደሚታወቅ እናምናለን። ማቴ 25:41 ፤ራእይ 20:7 – 10

18 የእሳት ባሕር

በመጨረሻ ወደ እሳት ባሕር የሚገባው ሠይጣንና መልአክቶቹ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ከተፈጠረ ጀምሮ የተወለዱት የሰው ልጆች ሁሉ ከሙታን በመነሳት የኅሊናን፣ የሙሴንና፣ የወንጌልን ሕግ ያልታዘዙ ሁሉ ለዘ ላለም ከሠይጣንና ከመላእክቶቹ ጋር በእሳት ባሕር የሚገቡበት የፍርድ ሂደት እንደሆነ እናምናለን። ራእይ 20:1 – 15

19 አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር

በ 1 ኛ ጴጥ 3:13 እና ራእይ 21:1 – 4 መሠረት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደሚፈጠርና የቀደመው ሠማይና ምድር እንደሚያልፍ እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ይህ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ለዘላለም የክርስቶስ ኢየሱስ እና የቅዱሳን መኖሪያ እንደሆነ እናምናለ ን። የአማኞች ሞትና የማያምኑት ሞት መጨረሻ በጌታ ያመኑት አማኞች ሞት መጨረሻ የሥጋ ሞት በሚሆንበት ጊዜ በክርስቶስ ኢየሱስ የድኅነት ሥራ ያመኑት እውነተኛ አማኞች ሁሉ ነፍሳቸው ወደ ገነት ( የእግዚአብሔር ኅልውና ወዳለበት ) እንደሚሄድ / ትሄድ እናምናለን። መክ 12:7 ፤ ሉቃ 23:43 ፤ ዮሐ 11:5 ፤ 1 ኛ ቆሮ 15:40 – 49 .

20 በኢየሱስ ማዳንና ስራው ያላመኑ

በጌታ በኢየሱስ ክርስ ቶስ የደኅንነት ሥራ ያላመኑትና እንደ ወንጌል ትምህርት ያልኖሩት ወደ ሲዖል ይሄዳሉ። ሲዖል ማለት ዳግም በጌታ ያላመኑ ሰዎች ነፍስ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ የምትቆይበትና ፈጽሞ እግ ዚአብ ሔር በ ቁ ጣው የ ሚ ገ ኝ በ ት ሥፍ ራ ነው። ማቴ 13:41 – 43 ፤ዮሐ 3:18, 36 ፤ ሮሜ 6:23 ፤ 1 ኛ ዮሐ 5:12

21 ጋብቻ

የ የቤተ ፋጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የአንድ ለአንድ ጋብቻ ማለትም በአንድ ወንድና በአንድ ሴት መካከል በሕይወት ዘመን ሁሉ አብሮ የሚሆኑበት የጋብቻ ቃል ኪዳን ሲሆን፤ በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በሌላ በማንኛውም መንገድ ፍቺ እንደማይፈጸም ታምናለች። ደግሞም ከሁለቱ አንዱ በሞት ካልተለዩ በስተቀር በሌላ በማንኛውም ምክንያት ዳግም ጋብቻን የ የቤተ ፋጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የማትቀበልና የማታስተናግድ መሆንዋን እናምናለን። ማቴ 5:31 – 32 ፤ ማቴ 19:4 – 9 ፤ ማር 10:2 – 12 ፤ ሉ ቃ 16:18 ፤ 1 ኛ ቆሮ 7:10 – 11 ፤ ዕብ 13:4

22 አምልኮና የቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና ሥርዓቶች

የ የቤተ ፋጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን እሁድና ሐ ሙስ ዋና የአምልኮ ስብሰባ የሚደረግባቸው ቀናት መሆኑን ስታምን በ እ ነዚህ ቀን ዋና ዋና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶችን ቃ ለ እ ግ ዚአብ ሔር ፣ ጸሎትን፣ ዝማሬን፣ መባና አስራትን፣ ጥምቀትና የ ጌ ታ እ ራት፣ የልጆች ቡራኬና የአገልግሎት ሹመት የሚደረግበትና እግዚአብሔር አብ በልጁ በ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና እርዳታ የሚደረግ የአምልኮ ቀን እንደሆነ ታምናለች።

23 መልአኮች

የ የቤተ ፋጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን መልአክት ሁሉ በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ፍጡራን መሆናቸውና በማንኛውም መንገድ እንደማይመለኩ ታምናለች፤ እነዚህ መላእክት በሁለት የሚከፈሉ ሲሆኑ፦ 1/ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ፍጹም ታማኝ መልአክትና 2/ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁ መልአክት ተብለው ይታወቃሉ።

እነዚህ ታማኝ መልአክት አገልግሎታቸው፤ እግዚአብሔርንና ኢየሱስ ክርስቶስን ማገልገል፣ ማምለክና ለቅዱሳን የእግዚአብሔርን መልእክት ማምጣት ማገልገል፣ ቅዱሳንን ከአጋንንት ጥቃት መጠበቅና ቅዱሳን ሲሞቱም ነፍሳቸውን ወደ ገነት መውሰድ ይሆናል። መዝ 34:7 ፤ ሉቃ 2:9 – 14 ፤ ሉቃ 16:22 በእግዚአብሔር ላይ ያመጹ መልአክት ትልቁ ተግባራቸው ኃጢአትንና አመጽን መፍጠር ሲሆን እነርሱ እንዳመጹ የ ሰው ልጆችን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ እንዲያምጹ በማድረግ ወደ ዘላለም ሲዖል ሰዎችን ለመውሰድ ሌት ተቀን መትጋት እንደሆነ እናምናለን። ማቴ 25:41 ፤ ሉቃ 10:18 ፤ ኤፌ 2:2, 4:27, 6:11 ፤ ራእይ 12:10, 20:10

24 ተግሣጽና ማስተካከያ

የቤተ ፋጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ምዕመኖቿ እግዚአብሔር በማይከብርበትና የቤተ ክርስቲያንን ምስክርነትን የሚያበላሸውን ነገር በግለሰብም ሆ ነ በቡድን ሲያደርግና ሲሰማበት ነገሮችን በጥንቃቄ በማጤንና በመመርመር ተግሣጽና ማስተካከያን ትሠጣለች፤ ( ማቴ 18;15 – 17 ፣ 1 ኛ ቆሮ 15;11) እነዚህ ተግሣጾችና ማስተካከያዎች ትኩረት የሚያደርጉባቸው ነገሮች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርትና የ ቤተ ፋጌ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የእምነት አቋም የሚያፋልስ ትምህርቶችን ማስተማር የሕይወት ቅድስናቸው ለምሳሌ፦ ዝሙት፣ ማመንዘርን፣ አልኮል መጠጦችን እ ና ሌ ሎች ሱስን የ ሚ ያ ስ ከት ሉ ነ ገ ሮችን፣ መጠቀምን መሸጥንም፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚለያይ የፖለቲካ አሳቦችን ማራመድ፣ ዘረኝነት ፣ ቡድን በመፍጠር ቤተ ክርስቲያንን የመለያየት አቋም፣ የቤተ ክርስቲያንን ሃብት ንብረት በሥውር ሆነ በግልጥ መቀማትን ለእግዚአብሔር ክብር የማይሆኑ ንግድ ሆነ ሥራ ውስጥ መሳተፍን የመሳሰሉትን ነገሮች አገልጋዮችና አባላቶቿ ከእንደነዚህ እንዲጠበቁ ለማድረግና እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ለ ማድረግ የሚሠጥ የተግሣጽና የማስተካከያ እምነት ይሆናል። ገላ 6:1 ፤ ዕብ 12:6 – 10 ፤ 1 ኛ ጴጥ 1:15 – 16 ፤ 1 ኛ ዮሐ 2:15 ይህ የተግሣጽና የመመለስ አቋም ተመካሪው በምክርና በተግሣጽ የማይስተካከል ከሆነ ከቤተ ክርስቲያኒቷ አገልግሎት እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ማስቆምና ከቤተ ክርስቲያኒቷ አባልነት እስከማገድ ድረስ ይሆናል።